About RHB

ስለ ክልሉ ጤና ቢሮ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በ 6 ማዕከላት ማለትም ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ጂንካ፣ ሳውላ እና ካራት ብዝሃ-ማዕከላት ሲዋቀር ጤና ቢሮ በጂንካ ማዕከል ተቋቋመ፡፡ ሴክተሩ የመካከለኛ ዘመን የጤናው ዘርፍ የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ውስጥ በተቀመጠው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መሰረት የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት መርሆችን በመከተል ህብረተሰቡን አሳታፊ ያደረገ የጤና ዘርፍ ስርዓት በመገንባትና አጠናክሮ በመቀጠል ዘላቂነት ያለው፣ ጥራቱን የጠበቀ እና ፍትሃዊ የሆነ የጤና አገልግሎትን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ማድረስ፣ የህብረተሰቡን የጤና ባለቤትነት የማረጋገጥ ስራን በጤና ልማት ሰራዊት የማጎልበት እና ከህብረተሰቡ ፍላጎት ጋር የሚሄድ ማህረሰብ-አቀፍ የጤና አገልግሎትን በሰፊው ለማስረጽ የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ የማስቀጠል ስራን እንደ ዋና ማስፈጸሚያ ስልት በማድረግ እየተገበረ ይገኛል፡፡

መሰረተ ልማት ገጽታ

በክልሉ ጤና ቢሮ ስር ያሉ ጤና ተቋማት
• የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
• የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
• 1 ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
• 2 ቅርንጫፍ ላቦራቶሪዎች
• 5 ደም ባንኮች (አንድ በግንባታ ላይ ያለ)
• 37 ሆስፒታሎች (31 የመንግስት ፡ 25 የመጀመሪያ ደረጃ ፤ 3 አጠቃላይ፤ 3 ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ) ) 6 የግልና መያድ ሆስፒታሎች
• 285 ጤና ጣቢያዎች
• 1,464 ጤና ኬላዎች
• ከ210 በላይ የተለያዩ የግል ክሊኒኮች

error: Content is protected !!
Scroll to Top