cbhi

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ.ም ንቅናቄ መድረክ ተጠናቀቀ

 

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ.ም ንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል።

በንቅናቄው መድረክ ላይ የሥራ መመሪያ የሰጡት የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል ህዝባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁላችንም የማዕጤመ አሰባሰብን በንቅናቄ መምራት አለብን ብለዋል።

አቶ ዘውዱ አክለውም የመድኃኒት አቅርቦት እና የተፈጠረውን የዋጋ ንረት ታሳቢ በማድረግ ማስተካከያ መደረጉን በመገንዘብ አመራሩ የማአጤመ መዋጮ በትኩረት ሊመራው ይገባል ብለዋል።

የተሠራጩ ደረሰኞች የመመለስ እና ጤና ተቋማትን ኦዲት የማድረግ ሥራ በልዩ ትኩረት እንደሚመራም የመንግስት ዋና ተጠሪው አስገንዝበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ በበኩላቸው የማዐጤመ ገቢ አሰባሰብን በሚመለከት አማራጮችን አሟጦ መጠቀም እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ለሥራው ስኬታማነት የሁሉም የጋራ ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

ዋናው የማዐጤመ አገልግሎት ሀብት በማስተባበር ሁሉም የጤና አገልግሎት ማስቻል እንደሆነ ገልጸው ሁሉንም አባል የማድረግ ሥራ ይሠራል ብለዋል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ በማአጤመ አፈጻጸም አባል ከማፍራት አንጻር በ2016 የበጀት ዓመት ዘጠና በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

ወደፊት በአንድ ቋት ገንዘብ ሲሰበሰብ የተሻለ
የጤና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ሲሉም ኃላፊው ተናግረዋል።

በጤና ጣቢያዎች እና በሆስፒታሎች የማአጤመ አገልግሎት መሻሻል ማሳየቱን በመግለጽ የመድኃኒት አቅርቦት ችግር አሁንም መስተካከል አለበት ሲሉ አቶ ፀጋዬ አሳስበዋል።

አያይዘውም በመድኃኒት አቅርቦት በኩል ያለውን ችግር ለመፍታት አመራሩ በትኩረት መሥራት አለበት ሲሉም አሳስበዋል ኃላፊው።

የማአጤመ ክፍያ ለከፈሉ አባላት ደረሰኝ የመስጠት እንዲሁም የመታወቂያ ካርድ የመስጠት ሥራ በትኩረት ሊመራ ይገባል ብለዋል አቶ ፀጋዬ።

ኦዲት መደረግ ያለባቸው ጤና ተቋማት በጊዜ ኦዲት ከማድረግ አንጻር እንዲሁም ጉድለት ባለባቸው ላይ የእርምት እርምጃ ከመውሰድ አንጻር ክፍተት መኖሩንም አቶ ፀጋዬ አንስተው በ2017 የበጀት ዘመን የተነሱ ጉድለቶችን በዕቅድ በመሥራት እንደሚፈቱ ገልጸዋል።

,ምንጭ

የወላይታ ዞን ጤና መመሪያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

error: Content is protected !!
Scroll to Top